ፕሬዚደንት ዶክተር ሙላቱ ከኤምቲኤን የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ

የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ከኤምቲኤን የስራ ኃላፊዎች ጋር ኩባንያው በኢትዮጵያ መሰማራት በሚችልበት ሁኔታ ተወያዩ።

በውይይቱ የኩባንያው ሀላፊዎች በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ውስጥ ለመሳተፍ ፍላጎት እንዳላቸው አስታውቋል።

ኩባንያው የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን በከፊል ወደ ግል ለማዞር እንቅስቃሴ መጀመሩን ተከትሎ በኢትዮጵያ የቴክኖሎጂው ዘርፍ ለመሰማራት ፍላጎት ማሳየቱ ተነግሯል።

ዶክተር ሙላቱ የመንግስት ድርጅቶቹ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ወደ ግል የማዞር ሂደቱ ነፃና ግልፅ በሆነ መንገድ የሚካሄድ እና የሀገሪቱን ተጨባጭ ሁኔታ ያገናዘበ እንደሚሆን ከኩባንያው ሀላፊዎች ጋር በተወያዩበት ወቅት ገልፀዋል።

እንዲሁም በፕራይቬታይዜሽን ሂደቱ በሌሎች ሀገራት የተከሰቱ ችግሮች እንዳይደገሙ በትኩረት እንደሚሰራ ገልጸዋል ፡፡( ምንጭ:የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት)