ከ9 ሀገራት የተውጣጡ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች የሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክን ጎበኙ

 ከዘጠኝ የውጭ ሀገራት የፖለቲካ ፓርቲዎች የተውጣጡ 32 የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች የሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክን ጎብኝተዋል።

የሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ፍፁም ከተማ ለጎብኚዎቹ ስለ አጠቃላይ ኢንዱስትሪ ፓርኩ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በማብራሪያቸውም የኢንዱስትሪ ፓርኩ ስለ ፈጠረው የስራ እድል፣ የወጪ ንግድ መር ስለመሆኑ እንዲሁም የኢትዮጵያን ወደ ኢንዱስትሩ ሽግግር ያረጋግጣል ተብው ከሚጠበቁ አንዱ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ከማብራሪያው በመቀጠልም ፓርኩ ስለሚሰጣቸው አገልግሎቶች፤ በተለየም የውሃ ማከሚያ ተቋሙ እና አንድ የተመረጠ ፋብሪካን ገብኝተዋል።

የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮቹ በትናንትናው እለት በተጀመረው 11ኛው የኢህአዴግ ድርጅታዊ ጉባዔ ላይ በእንግድነት ተጋብዘው የመጡ ናቸው።

የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮቹ የጅብቲው ገዥ ፓርቲ አር ፒፒ፣ የቻይናው ኮሚኒስት ፓርቲ ሲፒሲ፣ የኬንያው ገዥው ፓርቲ ጁብሊ፣ ሩዋንዳው ገዥ ፓርቲ አርፒኤፍ፣ የጀርመን የሶሻል ዲሞክራት ፓርቲ፣ የሱዳን፣ ታንዛኒያ የደቡብ አፍሪካ እና የታንዛኒያ ፖለቲካ ፓርቲ ናቸው። (ኤፍ.ቢ.ሲ)