የርብ የመስኖ ግድብ ፕሮጀክት በመጪው ጥቅምት 18 እንደሚመረቅ ተገለጸ

ከ3 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባው የርብ የመስኖ ግድብ ፕሮጀክት በመጪው ጥቅምት 18 በይፋ እንደሚመረቅ ተገለጸ ።

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት፣ በደቡብ ጎንደር ዞን አስተዳደር፣ በፋርጣና በእብናት ወረዳዎች መካከል የሚገኘው የርብ የመስኖ ግድብ ፕሮጀክት ለግንባታ ሥራው  3 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ወጪ ተደርጓል፡፡

የርብ የመስኖ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት 800 ሜትር ርዝመት እና 73 ነጥብ 5 ሜትር ከፍታ አለው፡፡ 234 ሚሊዮን ሜትር ኩብ ውሃ እንደሚይዝ እና 20 ሺህ ሄክታር መሬት በመስኖ የማልማት አቅም እንደሚኖረውም የውኃ፣መስኖና ኤሌክትሪክ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ግድቡ 20 ሺህ ሄክታር መሬት በመስኖ የማልማት አቅም አለው፡፡ ይህም በዓመት ሦስት ጊዜ ሰብል ለማልማት ያስችላል ነው ያለው ሚኒስቴሩ፡፡ (ምንጭ:የአማራ መገናኛ ብዙሃን ድርጅት)