ፕሬዚዳንት ቦሩት ፓሆር የኢትዮጵያ ጉብኝታቸውን ጀመሩ

የስሎቬኒያ ፕሬዝዳንት ቦሩት ፓሆር በኢትዮጵያ የሚያደርጉተን ይፋዊ ጉብኝት በይፋ ጀምረዋል።

በፕሬዚዳንቱ የተመራ የስሎቬኒያ የቢዝነስ ማህበረሰብ አባላትን ያቀፈው ልኡክ የሶስት ቀናት ጉብኝት ያደርጋል ነው የተባለው፡፡

ፕሬዚዳንት ቦሁር ዛሬ ከኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ጋር በሁለቱ ሀገራት ወቅታዊና የወደፊት የኢኮኖሚና ቢዝነስ፣ የፖለቲካ እንዲሁም የህዝብ ለህዝብ ትብብር ዙሪያ ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ሁለቱ ፕሬዝዳንቶች የጋራ አጀንዳ በሆኑ አካባቢያዊና አለምአቀፋዊ አጀንዳዎች ላይ በሚተባበሩበት ሁኔታ እንደሚመክሩም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

ፕሬዚዳነት ቦሩት በኢትዮጵያ ቆይታቸው በቀጣይ ቀናት ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤና ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ጋር ውይይቶች እንደሚያካሂዱም ይጠበቃል።

የስሎቬኒያ የቢዝነስ ማህበረሰብ አባላትም ከኢትዮጵያ የንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤትና ከቢዝነስ ማህበረሰብ አባላት ጋር ስለ ቢዝነስ አማራጮችና በአጋርነት መስራት ስለሚቻልበት ሁኔታ ውይይት ያካሂዳሉ።