ባለሥልጣኑ ከ 13ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የሚከናወኑ የስምንት መንገዶች ግንባታ ኮንትራት ስምምነት ፈጸመ

ከ13 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የሚካሄዱ 600 ኪሎሜትር የሚረዝሙ የስምንት የመንገዶች ግንባታ ሥራ ኮንትራት መፈጸሙን የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን አስታወቀ ።

የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን አቶ ሃብታሙ ተገኝ እንደገለጹት የሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን አካል የሆኑትና 600 ኪሎሜትር ርዝመት የሚሸፍኑትን የስምንት መንገዶች የግንባታ ሥራ ኮንትራት ስምምነት በሂልተን ሆቴል ፈጽመዋል ።        

መንገዶቹ ከዚህ በፊት በጠጠር ደረጃ የነበሩ ሲሆን አሁን ግን በአስፋልት ደረጃ የሚገነቡ ይሆናሉ። ለነዚህም ግንባታ ሙሉ ለሙሉ የኢትዮጵያ መንግስት የሚሸፈን ይሆናል።

የመንገዶቹ ግንባታ በሚጠናቀቅበት ወቅት እንደ ጤፍ ፣ማር እና ፍየል እንዲሁም ሌሎች የግብርና ምርቶችንም ሆነ ሌሎች ምርቶችን ካለምንም ችግር ወደ ገበያ ለማውጣት ያስችላሉ፡፡

በተጨማሪም ከዚህ በፊት በአካባቢው የነበረውን የተቀላጠፈ የትራንስፖርት ችግር በመቅረፍ የአካባቢው ህብረተሰብ በተመጣጣኝ ዋጋ ወደ ፈለገው ቦታ የሚንቀሳቀስበትን ሁኔታ ያመቻቻሉ፡፡

የመንገድ ፕሮጀክቶቹ  በአገሪቱ ካለው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ እንዲሁም መንግሥት ከያዘው የድህነትና የኋላቀርነት ቅነሳ ስትራቴጂ አንጻር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክቱ ይታመናል፡፡

የመንገዶቹ ግንባታ በሚጠናቀቅበት ወቅት ከዚህ በፊት በአካባቢው የነበረውን የትራንስፖርት ችግር በመቅረፍ የአካባቢው ህብረተሰብ በቀላሉ ወደ ፈለገው ቦታ የሚንቀሳቀስበትን ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥሩም ይጠበቃል ።

በኢንቨስትመንት የተሠማሩ ባለሃብቶች ያመረቱትን ምርት ወደ ገበያ ለማውጣት እንዲችሉና ሌሎች ባለሃብቶችም በአካባቢው ኢንቨስት ለማድረግ ተነሳሽነትን ከመፍጠር አኳያ የዚህ መንገድ መገንባት ጉልህ ሚና ይጫወታል፡፡

የመንገድ ኘሮጀክቶቹ በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቁ በአካባቢው የሚገኙ የመስተዳድር አካላትና፣ የክልሉ ነዋሪዎች ከፍተኛ ትብብር እንደሚያደርጉ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ያሳስባል፡፡

                      

የመንገድ ፕሮጀክቶቹ ዝርዝር መረጃ እንደሚከተለው ቀርቧል

1. ጣርማበር – መለያ – ሰፈሜዳ መገንጠያ1 መለያ – ሞላሌ – መገንጠያ 2 ሞላሌ – ወገሬ መንገድ ርዝመት 118.87 ኪ.ሜ
o የገንዘቡ መጠን 1,906,200,296.75 ብር
o የግንባታ ጊዜ ሚፈጀው 36 ወራት
o ኮንትራክተር መከላከያ ኮንስትራክሽን

2. ጂማ – አጋሮ – ዴዴሳ ወንዝ መንገድ ርዝመት 79.07 ኪ.ሜ
o የገንዘቡ መጠን 1,306,509,305.57 ብር
o የግንባታ ጊዜ ሚፈጀው 42 ወራት
o ኮንትራክተር ቻይና ሬል ዌይ 21ኛ ቢሮ ግሩኘ
o ቀድሞ የነበረው የመንገዱ ደረጃ አስፋልት

3. መሰል/ሞሲሊ – ኮራ/ቆሪ – 84.2 ኪ.ሜ /ኮንት 1/ መንገድ ርዝመት 84.2 ኪ.ሜ
o የገንዘቡ መጠን 1,536,235,563.54 ብር
o የግንባታ ጊዜ ሚፈጀው 42 ወራት
o ኮንትራክተር ቻይና ስቴት ኮንስትራክሽን ኢንጂነሪንግ ኮ.ሊሚትድ

4. መሰል/ሞሲሊ – ኮራ/ቆሪ – 84.2 – ጠሩ ኪ.ሜ /ኮንት 2/ መንገድ ርዝመት 73.34 ኪ.ሜ
o የገንዘቡ መጠን 1,502,371,329.85 ብር
o የግንባታ ጊዜ ሚፈጀው 42 ወራት
o ኮንትራክተር ቻይና ስቴት ኮንስትራክሽን ኢንጂነሪንግ

5. አርሲ – ሮቤ – አጋርፋ – አሊ ኮንትራት 1 አሊ ከተማ-ዋቤ ድልድይ መንገድ ርዝመት 53.5 ኪ.ሜ
o የገንዘቡ መጠን 2,153,060,671.98 ብር
o የግንባታ ጊዜ ሚፈጀው 36 ወራት
o ኮንትራክተር ቻይና ኮሙኒኬሽን ኮንስትራክሽን ኩባንያ(ሲሲሲሲ)

6. አዲአርቃይ – ጠለምት መንገድ ርዝመት 76.6 ኪ.ሜ
o የገንዘቡ መጠን 1,981,378,049.64 ብር
o የግንባታ ጊዜ ሚፈጀው 36 ወራት
o ኮንትራክተር የንኮማድ ኮንስትራክሽን

7. እስቴ – ስማዳ መንገድ ርዝመት 53.08 ኪ.ሜ
o የገንዘቡ መጠን 1,925,451,264.41ብር
o የግንባታ ጊዜ ሚፈጀው 36 ወራት
o ኮንትራክተር ቻይና ኮሙኒኬሽን ኮንስትራክሽን ኩባንያ(ሲሲሲሲ)

8. ውቅሮ – አጽቢ – ኮነባ መንገድ ርዝመት 63 ኪ.ሜ
o የገንዘቡ መጠን 1,745,722,493.86 ብር
o የግንባታ ጊዜ ሚፈጀው 42 ወራት
o ኮንትራክተር ሱር ኮንስትራክሽን