የገቢዎች ሚኒስቴር እና ጉምሩክ ኮሚሽን ራሳቸውን ችለው መደራጀታቸው ተገለጸ

የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን ራሳቸውን ችለው መደራጀታቸውን የገቢዎች ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

መልሶ የማዋቀሩ እና የማደራጀቱ ስራ የተሰራው ስራን ማዕከል ባደረገና ወጪን በሚቆጥብ መልኩ እነደሆነ የገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ አዳነች አበቤ ተናግረዋል፡፡

አዲሱ አደረጃጀት የተቋማቱን ተልዕኮ ውጤታማ ሊያደርግ በሚችል መልኩ እንደተሰራ ሚኒስትሯ ጠቁመዋል፡፡

በቅርቡ መንግስት የአስፈጻሚ አካላትን መልሶ የማደራጀት ስራ መስራቱን ተከትሎ የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን ራሳቸውን ችለው መደራጀት እንዳለባቸው መገለጹ ይታወሳል፡፡

የመዋቅር ማሻሻያው ዝርዝር መረጃ በቀጣይ የሚገለጽ እንደሚሆን ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡