ኢትዮጵያና አየርላንድ 330 ሚሊዮን ብር በላይ የድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ

 የአየርላንድ መንግስት  ለኢትዮጵያ  የ330 ነጥብ 87 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ለመሥጠት ስምምነት አደረገ  ፡፡

የድጋፍ ስምምነቱ በዝቅተኛ ኑሮ የሚተዳደሩ የህብረተሰብ ክፍሎችን የሚረዳውን የሴፍቲ ኔት መርሃ-ግብርን ለመደገፍ ያለመ መሆኑ ተገልጸዋል፡፡

የድጋፍ ስምምነቱ የኢፌዴሪ ገንዘብ ሚንስትር አቶ አህመድ ሺዴ እና በኢትዮጵያ የአይርላንድ አምባሳደር ሶንጃ አይላንድ ነው የተፈራረሙት፡፡ (ምንጭ፦ የገንዘብ ሚኒስቴር)