ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የአርሶአደር ማሳ እየጎበኙ ናቸው

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሞረትና ጅሩ ወረዳ የአርሶአደሩን የስንዴ ሰብልን በመጎብኘት ላይ ናቸው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በመገኘት በሞረትና ጅሩ ወረዳ በኩታ ገጠም የተዘራ የስንዴ ሰብልን ለመጎብኘት ወደ ሥፍራው ማቅናታቸው ነው የተገለጸው፡፡

ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ጋር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችም ሰብሉን እየጎበኙ መሆናቸውም ታውቋል፡፡

በሞረትና ጅሩ ወረዳ በሔክታር እስከ 60 ኩንታል ስንዴ እንደሚመረት ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አካባቢውን ከጎበኙ በኋላ ከአርሶ አደሮች ጋር እንደሚወያዩም ነው የሚጠበቀው፡፡ (ምንጭ፡- አማራ መገነኛ ብዙሓን)