በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ የነበረ ናፍታ በቁጥጥር ሥር ዋለ

በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ የነበረ ናፍታ በቁጥጥር ሥር መዋሉን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ። 

በገቢዎች ሚኒስቴር የጉምሩክ ኮሚሽን የጅግጅጋ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የህግ ተገዢነት ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ አህመድ መሀመድ እንዳስታወቁት፥ በህገ ወጥ መንገድ ናፍታ ጭነው ሲንቀሳቀሱ የነበሩት ተሽከርካሪዎች በሱማሌ ክልል ነው በቁጥጥር ስር የዋሉት።

ነዳጅ ጭነው ሲጓዙ የነበሩ መኪናዎች አሽከርካሪዎችም በቁጥጥር ሥር መዋላቸውንም አቶ አህመድ አስታውቀዋል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የነዳጅ ፍላጎትና አቅርቦት ካለመመጣጠን ጋር በተያያዘ በየነዳጅ ማደያዎች ረጃጅም ሰልፎችን መመልከት እየተለመደ መጥቷል።

ለዚህም በምክንያትነት ከሚጠቀሱት ውስጥ ህገ ወጥ የነዳጅ ንግድ አንዱ ሲሆን፥ ተገቢ ያልሆነ ውድድር እና የሎጀስቲክስ አቅርቦቱ ምቹ አለመሆን የዘርፉ ችግሮች በመሆን ይጠቀሳሉ።(ኤፍቢሲ)