የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም ለኢትዮጵያ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለጸ

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም ለኢትዮጵያ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለጸ፡፡

የኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ሂሩት ዘመነ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም አንደር ሴክሬታሪ ጀነራል ኃላፊ ሚስተር አችሚን ስታይነር ጋር በጽህፈት ቤታቸው ተወያይተዋል።

ኢትዮጵያ አረንጓዴ ልማትን በመተግበር የዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት እና የዴሞክራሲ ሥርዓትን በመገንባት ሂደት ከፍተኛ ርብርብ እያደረገች እንደሆነና በዚህም ሁሉን አቀፍ ውጤት እያስመአዘገበች እንደምትገኝ ሚኒስትር ዴኤታዋ ወ/ሮ ሂሩት ገልፀዋል።

ሚስተር አችሚን በበኩላቸው በኢትዮጵያ በመተግበር ላይ ያለውን ሁሉን አቀፍ ለውጥ አድንቀው የተባበሩት መንግስታት የልማት ድርጅት ፕሮግራም በኢትዮጵያ የተጀመረውን ሪፎርም ለማስቀጠል ድጋፉን አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም በኢትዮጵያ የዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት በሚደረገው ርብርብ ላይ ከፍተኛ ድጋፍ የሚያደርግ የኢትዮጵያ ዋነኛ የልማት አጋር መሆኑ ይታወቃል። (ምንጭ፡-የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃልአቀባይ ጽህፈት ቤት)