ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከተመድ የልማት ፕሮግራም አስተዳዳሪ አቺም ስታይነር ጋር ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም አስተዳዳሪ አቺም ስታይነርና የልዑካን ቡድናቸውን  በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በውይይታቸው ወቅት የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም ለኢትዮጵያ የዲሞክራሲያዊ አስተዳደር መጠናከር፣ የአቅም ግንባታ፣ የኢኮኖሚ እድገትና የድህነት ቅነሳን በማፋጠን እንቅስቃሴዎች ዙሪያ ለረጅም ጊዜ የቆየ የቴክኒክና የገንዘብ ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱን እንደሚያደንቁ ገልጸዋል፡፡

እንደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለፃ መንግስታቸው ይህንኑ አጋርነት ለማጠናከር እንደሚሠራ አስታውቀዋል ። 

የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም አስተዳዳሪ አቺም ስታይነር በበኩላቸው የኢትዮጵያ መንግስት በዶክተር አብይ አህመድ አመራር ስር እየወሰደ ያለውን የዲሞክራሲያዊ ለውጥ ሂደት አድንቀው የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራምም ትብብሩን  አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል፡፡ (ምንጭ : የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት )