በምስራቅ ሸዋ ዞን ሉሜ ወረዳ ጆቦ ቀበሌ በተሽከርካሪ ላይ ዛሬ በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ 90ሺህ የአሜሪካ ዶላር መያዙን ፖሊስ አስታወቀ፡፡
የዞኑ ፖሊስ መምሪያ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር አስቻለው ዓለሙ እንደገለጹት ዶላሩ የተያዘው ከአዲስ አበባ ወደ አዳማ ሲጓዝ በነበረ የታርጋ ቁጥሩ ኮድ 3- 5124 ኦሮ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ውስጥ ነው፡፡
ተሽከርካሪው ለድንገተኛ ፍተሻ ሲቆም ህገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር ለማድረግ የሞከረው ግለሰብ ዶላሩን የያዘበትን ቦርሳ ጥሎ ያመለጠ ቢሆንም ፖሊስ ክትትል እያደረገ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴ፣ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያና የገንዘብ ዝውውርን ለመቆጣጠር በተለያዩ የዞኑ አካባቢዎች ኬላዎች መቋቋማቸውን የጠቀሱት ከማንደሩ ህብረተሰቡ ህገ ወጥ ድርጊትን ለመከላከል ለፖሊስ እያሳየ ያለውን ትብብር አጠናክሮ እንዲቀጥልም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ (ኢዜአ)