የኢትዮጵያ ሲቪል አቪየሽን ባለስልጣን ለ397 ባለሙያዎች የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ሰጠ

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪየሽን ባለስልጣን ለ397 ባለሙያዎች የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ መሥጠቱን አስታወቀ፡፡

ባለስልጣኑ ባለፉት ስድስት ወራት ለ397 የአቪየሽን ባለሙያዎች አዲስ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ መሥጠቱን ገልጿል፡፡

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ለ216 አውሮፕላን አብራሪዎችና ለ163 አውሮፕላን ቴክኒሻኖች አዲስ የብቃት ማረጋገጫ መሥጠቱን አስታውቋል።

ለ3 ሺህ 24 ባለሙያዎች ደግሞ የሙያ ፈቃድ እድሳት እያደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ ሲቪል አቪየሽን ባለስልጣን የህዝብ ግንኙነት ሥራ አስኪያጅ አቶ አንሙት ለማ ተናግረዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ለ1 ሺህ 443 የበረራ ሠራተኞች የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ዕድሳት መሥጠቱንም ገልጸዋል፡፡ (ኤፍ.ቢ.ሲ)