ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ ከዓለም ባንክ ጊዚያዊ ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ

 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ከዓለም ባንክ ጊዜያዊ ፕሬዚዳንት ክሪስታሊና ጆርጂዬቫ ጋር ተወያዩ።

በውይይታቸው ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ እያደረገ ያለውን ቴክኒካዊ እና የገንዘብ ድጋፍ አድንቀዋል።

ባንኩ እያደረገ ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ በሚቀጥልበትና ወደፊት በሚተገበሩ አዳዲስ ፕሮጀክቶች ዙሪያም ውይይት አድርገዋል።

የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ የልማት አጋር ሲሆን፥ የገንዘብና የተለያዩ ቴክኒካዊ ድጋፎችን በማድረግ በኢትዮጵያ የሚካሄዱ የልማት ስራዎችን ይደግፋል።(ምንጭ:የጠቅላይ ሚንስትር ጽህፈት ቤት)