ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከዓለም ኢኮኖሚ ፎረም ጉባኤ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ክላውስ ሽዋብ ጋር ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከዓለም ኢኮኖሚ ፎረም ጉባኤ መስራችና ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ክላውስ ሽዋብ ጋር ተወያዩ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩና ሊቀመንበሩ በዳቮስ እየተካሄደ ካለው የዓለም ኢኮኖሚ ፎረም ጉባኤ ጎን ለጎን ነው ውይይት ያደረጉት፡፡

በውይይታቸው ወቅትም ዓለም አቀፍ ፈተናዎችን ለመፍታት በንግድ፣ በመንግስትና በግሉ ዘርፍ እንዲሁም በሲቪክ ማህበረሰቡ የሚኖር የተቀናጀ አሰራር አስፈላጊነት ላይ መክረዋል።

ኢትዮጵያም በፈረንጆቹ 2020 የዓለም ኢኮኖሚ ፎረምን እንድታስተናግድም በውይይታቸው ወቅት ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡

በትናንትናው እለት ስዊዘርላንድ ዳቮስ የገቡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከጉባኤው ጎን ለጎን የሁለትዮሽ ውይይቶችን አድርገዋል፡፡

በዛሬው እለትም ከዓለም ባንክ ጊዜያዊ ፕሬዚዳንት ክሪስታሊና ጆርጂዬቫ ጋር መወያየታቸው የሚታወስ ነው፡፡ (ምንጭ፡-የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት)