ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የኦሞ ኩራዝ 3 የስኳር ልማት ፕሮጀክትን ጎበኙ

የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በደቡብ ክልል በቤንች ማጂ ዞን የኦሞ ኩራዝ ~ 3 የስኳር ልማት ፕሮጀክት ጎብኝተዋል።

የኦሞ ኩራዝ ~ 3 የስኳር ልማት ፕሮጀክት በሙሉ አቅም የማምረት ሽግግር ሂደት ውጤታማ እንደሆነ የፕሮጀክቱ የስራ ሃላፊዎች ገለፃ አድርገውላቸዋል።

የኦሞ ኩራዝ ~ 3 የስኳር ልማት ፕሮጀክት በቀን 12 ሺህ ኩንታል ስኳር የማምረት ብቃት ላይ መድረሱን ባለሙያዎች አስረድተዋል።

ፕሮጀክቱ በሙሉ አቅም የስኳር ምርት ደረጃ ላይ መድረሱን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ አድንቀው፥ ለፕሮጀክቱ ዘላቂ ውጤታማነት ባለሙያዎች በተሻለ ጥረት እንዲሰሩ አበረታተዋል።

ከጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ ጋር በመሆን የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ የመንግስት ስራ ሃላፊዎች የኦሞ ኩራዝ ~ 3 የስኳር ልማት ፕሮጀክትን ጎብኝተዋል። (ምንጭ፡-የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት)