በአማራ ክልል ግብር አሰባሰብ ላይ መግባባትን ለመፍጠር ውይይት እየተካሄደ ነው

በአማራ ክልል የታክስ አምባሳደሮች የተሳተፉበት ግብር አሰባሰብ ላይ መግባባት መፍጠርን አላማው ያደረገ ውይይት በባህርዳር ከተማ በመካሄድ ላይ ነው፡፡

የመድረኩ ዋና ዓለማ በግብር ግንዛቤ አስተዳደር እና ግብር አሰባሰብ የጋራ ግንዛቤ መፍጠር ላይ ትኩረት እንደሚደረግ ነው የተገለፀው።

ከለውጡ ጋር ተያይዞ የመጣውን የህብረተሰቡ የመልማት ጥያቄ ለመመለስ የሚያስችል የፋይናንስ ስርዓት ለመፍጠር ከለውጡ ጋር የመጡ የተዛቡ አስተሳሰቦችን እና ድርጊቶችን መቅረፍ በዋናነት የሚታዩ ጉዳዮች እንደሆኑም ተጠቁሟል።

ግብር የሚሰበስቡ እና የሚያስከፍሉ አካላት ወደ ግብር ከፋዩ ህብረተሰብ ዘንድ በሚቀርቡበት ጊዜ አልተደመርክም ወይ የሚል ግብር መሰብሰብ ከአዲሱ ስርዓት ጋር የሚሰራ አድርጎ የመገንዘብ ሁኔታዎች ለታክስ ስርዓቱ ከፍተኛ ችግር መሆናቸው ነው በመድረኩ ላይ የተገለፀው።

በመድረኩ የክልሉ ርእሰ መስተዳድር ዶ/ር አምባቸው መኮንንና የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ ብዙአየሁ ቢያዝንን ጨምሮ ከፍተኛ አመራሮችና ከክልሉ ሁሉም ዞኖችና ወረዳዎች የተውጣጡ የታክስ አምባሳደሮች ተገኝተዋል። (ኢቲቪ)