በ899 ድርጅቶች ላይ የሒሳብ ጉድለት መገኘቱ ተገለፀ

በ899 ድርጅቶች ላይ የሒሳብ ጉድለት መገኘቱን የጉምሩክ ኮሚሽን አስታወቀ።

በጉምሩክ ኮሚሽን ድህረ እቃ አወጣጥ ኦዲት ስነስርዓት ላይ የጉምሩክ ኮሚሽን ዳይሬክተር ወይዘሮ አለምጸሀይ ሀይሉ እንደገለጹት፥ የስራ ክፍሉ ባለፉት ስምንት ወራት ሶስት ኦዲቶችን ተከናውነዋል።

እነዚህ የኦዲት አይነቶችም የመስክ፣ ዴስክ እና አጠቃላይ ኦዲት መሆናቸው ነው የተገለፀው።

በአጠቃላይ በ2 ሺህ 78 ድርጅቶች ላይ ኦዲት መደረጉን የገለፁት ዳይሬክተሯ፥ ከዚህ ውስጥም በ899 ድርጅቶች የኦዲት ግኝት ተገኝቶባቸዋል ብለዋል።

ባለፉት ስምንት ወራት ኦዲት ከተደረጉ ድርጅቶች 1 ነጥብ 24 ቢሊየን ብር የሒሳብ ጉድለት የተገኘ ሲሆን፥ ውዝፍ እዳን ጨምሮ 257 ነጥብ 53 ሚሊየን ብር ወደ ገንዘብ መቀየሩን ዳይሬክተሯ ገልፀዋል፡፡

የሒሳብ ጉድለት የተገኘባቸው ድርጅቶች በኦዲቱ የተገኘውን ገንዘብ ገቢ እንዲያደርጉ የተወሰነባቸው ሲሆን፥ በቀጣይ አስተዳደራዊ እና ህጋዊ እርምጃዎች መውሰድ እንደሚጀመር ታውቋል፡፡       

(ምንጭ፡- ከገቢዎች ሚኒስቴር)