ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የቻይና ሬልዌይ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ኃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል፡፡
ኮርፖሬሽኑ ኢትዩጵያና ጂቡቲን የሚያገናኘዉን የባቡር ፕሮጀክት ላይ ተሳታፊ እንደነበሩ ተገልጿል::
በቀጣይነትም የአግሮ ፕሮሰሲንግ ኢንዱስቱሪ ፓርክ ግንባታና የነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ልማት ፕሮጀክቶች ላይ ለመሳተፍ ፍላጎታቸዉን አሳይተዋል::
እንዲሁም የሸገርን ማስዋብ ፕሮጀክት ላይ እንደሚካፈሉ ማሳወቃቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል::