ለኃይል ማሠራጫና ማከፋፈያ መሥመር ዝርጋታ የ1.8 ቢሊየን ዶላር ኢንቨስትመንት ስምምነት ተደረገ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ከቻይና የስቴት ግሪድ ኩባንያ ጋር ያደረጉትን ውይይት ተከትሎ ለኃይል ማሠራጫና ማከፋፈያ መሥመር ዝርጋታ የሚውል የ1 ነጥብ 8 ቢሊየን ዶላር ኢንቨስትመንት ስምምነት ፊርማ ተደርጓል። 

ስምምነቱ ለ16 የኢንዱስትሪ ፓርኮች፣ ለሁለተኛው የአዲስ ጅቡቲ የባቡር መስመርና ለተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ለማዳረስ የሚያስችል ነው። በዚህም ያልተቋረጠ የኤሌክትሪክ ኃይል ከማቅረብ በተጨማሪ ሥራ ለመፍጠርም ይረዳል መባሉን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።