ቻይና ለሸገር ማስዋብ ፕሮጀክት ግንባታ የፋይናስ ድጋፍ ለማድረግ ተስማማች

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከቻይናው ጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ኬኪያንግ ጋር የኢትዮ ቻይናን ግንኙነት የበለጠ በማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ውይይት አድርገዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ኬኪያንግ ቻይና ኢትዮጵያ የዜጎቿንና የኢኮኖሚዋን ደኅንነት ለማስቀጠል የምታደርገውን ጥረት እንደምትደግፍ ተናግረዋል፡፡

ሁለቱ ጠቅላይ ሚኒስትሮች ይህንኑ ትብብር የሚያጠናክሩ አምስት ስምምነቶች እንዲፈረሙ አድርገዋል::

የተፈረሙት ስምምነቶችም የሸገርን ማስዋብን ፕሮጀክት 12 ኪሎ ሜትር የወንዝ ዳርቻዉ ለመገንባት የፋይናንስ፣ የቴክኒክ

ትብብር እና የምግብ እርዳታ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

እንዲሁም ለቤልት ኤንድ ሮድ ማዕቀፍ የአምስት አመት ትብብር እቅድ እና የቻይና አፍሪካ የትብብር መድረክ (FOCAC) ስር የሚካሄድ ትብብር መተግበሪያ መግባቢያ ሰነድ ላይ መፈራረማቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡