የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ከማዕድን ፈላጊ ኩባንያዎች ጋር ተፈራረመ

የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር በተለያዮ የሀገሪቱ ክፍሎች የማዕድን ፍለጋ ለማካሄድ ፍቃድ ከተሰጣቸው ከሶስት ኩባንያዎች ጋር በዛሬው ዕለት ስምምነት ተፈራረመ፡፡

ኩባንያዎቹም በአማራ፣ በትግራይና በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ላይ በወርቅ፣ ብረትና ብረት ነክ እንዲሁም በከሰል ማዕድናት ምርመራ ያካሂዳሉ ተብሏል፡፡

በ31 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር የማዕድን ፍለጋ የሚያከናውኑት ኩባንያዎቹ ሁለቱ ሀገር በቀል ሲሆኑ አንዱ ደግሞ የቻይና ኩባንያ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

ስምምነቱንም የማዕድንና ነዳጅ ሚንስትር ዶክተር ሳሙኤል ኡርካቶና የሶስቱ ኩባንያ ዋና ስራ አስፈፃሚዎች ፈርመውታል፡፡

የስምምነቱ ውል ለሶስት ዓመታት የሚቆይ ሲሆን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱም ውሉን በፈለገበት ጊዜ ማደስ ይችላል ተብሏል፡፡