የዓለም ባንክ ፕሬዝዳንት ዴቪድ ማልፓስ ኢትዮጵያን ይጎበኛሉ

የዓለም ባንክ ፕሬዝዳንት ዴቪድ ማልፓስ በነገው ዕለት ለጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ፡፡

ፕሬዝዳንቱ ከኢትዮጵያ በተጨማሪ በማዳጋስካር፣ ሞዛምቢክ እና ግብጽ ጉብኝት እንደሚያደርጉ የባንኩ ቃል አቀባይ ገልጸዋል፡፡

አዲስ የተመረጡት ዴቪድ ማልፓስ የአለም ባንክ ለአፍሪካ የተለየ ትኩረት እንደሚሰጥ ገልጸዋል።

የዓለም ባንክ እና ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም /አይ ኤም ኤፍ/ በያዝነው የፈረንጆቹ ሚያዝያ ወር ላይ አፍሪካ ላይ ትኩረት የሚያደርግ ጉባኤ ያካሄዳሉ ተብሏል፡፡

በጉባዔው በአውሮፓውያኑ 2030 በአፍሪካ የከፋ ድህነትን ለማጥፋት በተቀመጠው ግብ ላይ ትኩረት በማድረግ ይመክራሉም ነው የተባለው፡፡ (ምንጭ፡-ሮይተርስ)