ሁለተኛው ቀን የቤልት ኤንድ ሮድ ጉባኤ እየተካሄደ ነው

ሁለተኛው ቀን የቤልት ኤንድ ሮድ ጉባኤ እየተካሄደ ነው፡፡

በጉባኤ የመሪዎች የንግግር መድረክ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ይህ ማህቀፍ በጋራ የፓሊሲ አግባብን ለመበየን፣ ለመሠረተ ልማት፣ ለንግድ፣ ለፋይናንስና የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት መልካም ዕድልን የሚፈጥር ነው ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአፍሪካ ቀንድ ቀጣና የፓለቲካ ስኬትን በማስፈን ዙሪያ የበለጠ የመሠረተ ልማት ለማስፋፋት፣ በረጅም ጊዜ በሚከፈል የፋይናንስ አቅርቦትና በመንግሥትና በግል ዘርፍ ጥምረት ዙሪያ እገዛ ጠይቀዋል፡፡

(ምንጭ፡-የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት)