የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ የሚያደርገውን ድጋፍ እንደሚቀጥል አረጋገጠ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የዓለም ባንክ ፕሬዝዳንት ዴቪድ ማልፓስንና ልዑካቸውን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ::

በሚያዝያ ወር አጋማሽ የዓለም ባንክ ፕሬዝዳንት ሆነው የተመረጡት ዴቪድ ማልፓስ ሦስት የአፍሪካ ሀገራትን በመጎብኘት ላይ ይገኛሉ::

ኢትዮጵያ እያካሄደች ያለውን የኢኮኖሚ ማሻሻያ ያደነቁት ፕሬዝዳንቱ የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ የሚያደርገውን ድጋፍ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል::

(ምንጭ፡-የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት)