የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለ“ሸገር ማስዋብ” ፕሮጀክት 500 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባን ጽዱና አረንጓዴ በማድረግ ቱሪዝምን ለማስፋፋት ለተነደፈው “ሸገርን ማስዋብ” ፕሮጀክት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የግማሽ ቢሊየን ብር ድጋፍ አደረገ።

የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ የብር 500 ሚሊየን ድጋፍ ለማድረግ የወሰነው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ ለባለሀብቶችና ለተቋማት ያደረጉትን የድጋፍ ጥሪ ተከትሎ ነው።

ባንኩ ወደፊትም የከተማዋን ገጽታ በማስዋብና በማሻሻል ነዋሪዎቿን ተጠቃሚ በሚያደርጉ መሰል ፕሮጀክቶች ላይ በመሳተፍ አገራዊ ኃላፊነቱን እንደሚወጣ ገልጿል።

(ምንጭ፡-የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)