በአዲስ አበባ የኤሌክትሪክ ኃይል የፈረቃ ስርጭት ላይ ለውጥ ተደረገ

በኤሌክትሪክ ኃይል እጥረት ምክንያት አዲስ አበባ የምታገኘው የኤሌክትሪክ የፈረቃ ስርጭት በአዲስ መልክ መከለሱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ፡፡

ቀደም ሲል ተግባራዊ ለማድረግ ተሞክሮ የነበረው ሶስት ፈረቃ ለአሰራር ምቹ ባለመሆኑ ዳግም ተከልሶ በሁለት ፈረቃ እንዲሆን መደረጉ ነው የተገለጸው፡፡

በዚህም መሰረት ከንጋቱ 11:00 እስከ ቀኑ 8:00 እና ከቀኑ 8:00 እስከ ምሽቱ 4:00 እንዲሆን የተደረገ ሲሆን፣ ሁለቱ የፈረቃ ሰዓቶች በመቀያየር አገልግሎት ላይ እንደሚውል ታውቋል፡፡

በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎችም ያለውን መርሀ ግብር፣ በዲስትሪክትና አገልግሎት መስጫ ጽህፈት ቤቶች አማካኝነት የሚገለጽ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል።