”የምንናገረዉን በተግባር ሆነን መገኘት መቻል አለብን” – ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

በፍላጎት ላይ የተመሰረተ የግብር ህግ ተገዥነትን ለማረጋገጥ የገቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስትሮችና ከፍተኛ አመራሮች ከዘረፉ ተዋናዮች ጋር እየተወያዩ ነዉ፡፡

ዉይይቱን በንግግር የከፈቱት የገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ግብርን በፍላጎት የመክፈል ባህልን በማዳበር በጋራ ተጠቃሚ የምንሆንበትን ለዉጥ ማምጣት ይገባል ብለዋል፡፡

ሚኒስትሯ አያይዘውም የግብር ጉዳይ የሁሉም የጋራ ኃላፊነት በመሆኑ የሚናገረዉን በተግባር አድርጎ ሆኖ መገኘት መቻል አለበት ነዉ ያሉት፡፡

ሚኒስቴሩ እያደረገ ባለዉ ሃገር አቀፍ የታክስ ንቅናቄ በጎ ዉጤቶች እያመጣ መሆኑንና ግብር የመክፈል ባህል ኋላ ቀር በመሆኑ የሚጠበቀው ለዉጥ እንዲመጣ ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ ወ/ሮ አዳነች ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የዉይይት መድረኩን የመሩት የታክስ አምባሳደሯ ህክመት አብደላ በበኩላቸው የአገሪቱን የታክስ ችግር ለመቅረፍ ወደኋላ ካሉ ችግሮች ይልቅ ወደ ፊት ሊገጥሙን የሚችሉ ተግዳሮቶችን እንዴት ልንፈታ ይገባል የሚለዉ ጉዳይ ላይ በትኩረት መስራትና መወያየት እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡