52ኛዉ የአፍሪካ የአየር ትንበያ ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነዉ

በኢጋድ የአየር ትንበያ ልዩ ማዕከል የሚዘጋጀዉ የአፍሪካ የአየር ትንበያ ጉባኤ በኢትዮጵያ አዘጋጅነት ለ52ኛ ጊዜ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነዉ፡፡

በጉባኤዉ ላይ ተገኝተዉ መልእክት ያስተላለፉት የዉሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ኢትዮጵያ በአፍሪካ የድርቅና የአየር ንብረት ተጠቂ ከሆኑ አገራት አንዷ መሆኗን አመልክተዋል፡፡

ችግሩን ለመቅረፍም የአየር ትንበያ ዘርፍን ለማዘመንና ተደራሽ ለማድረግ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

የአለም አቀፍ የአየር ትንበያ ማዕከል ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ማኪስ ዲሊ በበኩላቸዉ የአየር መዛባት የአገራትን ፖሊሲና የያዙትን ስትራቴጂ ከመጉዳቱም ባሻገር ድንገተኛ አደጋዎችን በመፍጠር የከፋ አደጋ በማድረስ ላይ እንደሚገኝ አዉስተዋል፡፡

የዉይይት መድረኩም ችግሩን ለመከላከል ግብአት የሚሆኑ ሰፊ ግብአቶችን እንደሚያስገኝ ተናግረዋል፡፡

በአፍሪካ በየአመቱ 24 ሚሊየን ሰዎች ለድርቅ እንደሚጋለጡና ከዚህም 12.5 ሚሊየን የሚሆኑት የምስረቅ አፍሪካ ነዋሪዎች መሆናቸዉ ታዉቋል፡፡