የግብር ስርአቱ ላይ መሰረታዊ ለዉጥ ማምጣት አለብን – ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን ጠቅላይ አቃቤ ህግን ጨምሮ ከሌሎች የፍትህ ተቋማት ጋር በጋራ በመሆን በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ የግብር ስርአቱ ላይ መሰረታዊ ለዉጥ ለማምጣት ኦዲት ላይ ያለውን ችግር እናስተካክላለን ብለዋል፡፡

በመድረኩ 3 ሺህ የሚሆኑ የንግድ ማህበረሰብ ጋር በገቢ አሰባሰብ ስርአቱ ላይ ያተኮረ የምክረ ሃሳብ ውይይት ተካሂዷል፡፡

የከተማዋ ገቢዎች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሺሰማ ገብረስላሴ እንደተናገሩት ከተማ አሰተዳደሩ ባለፉት አስራ አንድ ወራት 31 ነጥብ 79  ገቢ ለመሰብሰብ አቅዶ 29 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር ገቢ ሰብሰቧል፡፡

ባለፉት አስር ወራት 97 በመቶ ግብር ከፋች ግዴታቸዉ በመጣታቸው የግብር ማደሻ ክሊራንስ ወስዷል ብለዋል፡፡

ግብር አለመክፈል የሂሳብ ሰነዶች በትክክል እና በግልፅ አለመያዝ ደረሰኝ አለመሰጠት እና ሀሰተኛ ደረሰኝ ማቅረብ በመታየታቸው የከተማዋ ገቢ አሰባሰብ ዉጤታማ የታክስ አስተዳደር ባህርያትን ያሟላ ያሳያል ተበሏል፡፡ በተላይ የንግድ ማህበረሰቡ ከኮንትሮባንድ መቆጣጠር እና ከኦዲት ጋር ተያይዞ ሰፊ ችግር መኖሩን ጠቁመዉ ፋተሻ ሊደረግ ይገባል ብሏል፡፡

በተያያዘ 1 ሺህ 077 በተለያዩ ደረጃ የነበሩ ክሶች ከጠቅላይ አቃቤ ህግ ጋር በመነጋገር ካሶች እንዲቋረጡ ተደርጓል እንዲሁም ከ62 ሚልየን ብር በላይ በቅጣት መሰብሰቡን ታውቋል፡፡