በ2010 በጀት ዓመት ኦዲት 129 የኦዲት ግኝት መታየቱ ተገለጸ

በ2010 በጀት ዓመት ኦዲት ከተደረጉ 174 ተቋማት መካከል በ129ኙ የኦዲት ግኝት መታየቱ ተገለጸ፡፡

የገንዘብ ሚንስቴር በ2010 ዓ. ም በጀት አመት የዋና ኦዲተር ሪፖርት ላይ ከፌደራል መስሪያቤቶችና ከዩኒቨርሲቲዎች ከተዉጣጡ የፋይናንስ ዘርፍ አመራሮች ጋር ዉይይት አካሂዷል፡፡

በበጀት አመቱ ለተመዘገበዉ የጎላ የበጀት ክፍተት ዋና ዋና ምክንያቶች  የጥሬ ገንዘብ ጉድለት፣ በወቅቱ ያልተሰበሰበ ሂሳብ፣ የገቢ ሂሳብ አለመሰብሰብና በገቢ ሂሳብ ሪፖርት ዉስጥ አለማካተት እና የተሟላ ወጪ ማስረጃ ሳይቀርብ በወጪ ሂሳብ መመዝገብ ናቸዉ፡፡

በ2010ዓ. ም 174 መስሪያ ቤቶች ኦዲት የተደረጉ ሲሆን 129 የኦዲት ግኝት ታይቶባቸዋል፡፡ ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ከፍተናዉን የጥሬ ገንዘብ ጉድለት ማስመዝገቡ በመድረኩ ተነግሯል፡፡

በ9 መስሪያ ቤቶች 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ማስረጃ ባለመቅረቡ የተሰበሰበዉን ሂሳብ ትክክለኛት ማረጋገጥ አለመቻሉንም በዉይይቱ ላይ ተነስቷል፡፡

በ11 መስሪያ ቤቶች 52 ሚሊየን 054 ሺህ 783 ብር ከተወሰደ ተሰብሳቢ ሂሳብ ዉጭ ሆኖ ተገኝቷል፡፡