ኤጀንሲዉ በሀገሪቱ ያለውን የአፈር ሁኔታ የሚያሳዩ መረጃዎችን ሰበሰበ

የግብርናና ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲ በሀገሪቱ ያለውን የአፈር ሁኔታን የሚያሳዩ መረጃዎችን  በማእከላዊ የመረጃ ቋት ማሰባሰቡን የኤጀንሲው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ካሊድ ቦምባ ተናግረዋል።

በዚህ የመረጃ ማሰባሰብና የጥናት ሂደትም በወረዳና በቀበሌ ደረጃ የአፈር ለምነትና ለአፈሩ የሚያስፈልገው የማዳበሪያ አይነት በካርታ በተደገፈ መልኩ ለአብዛኛው ክልሎች መድረሱን የገለፁት ዋና ስራ አስፈፃሚው።

የዚህ የመረጃ ማሰባሰብና የጥናት ሂደትም 95 በመቶ መጠናቀቁንና ቀሪዎቹ እስከ መስከረም እንደሚጠናቀቁ ተናግረዋል።

የዚህ ጥናት ዋና አላማው በሀገሪቱ ዘላቂነት ያለው ምርታማነትን ማምጣት እንደመሆኑ መጠን ከተለያዩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር በመሆን መስራት እንደሚያስፈልግና ፡አርሶ አደሩን ተጠቃሚ እንዲሆን በማድረግ አፈርን መጠበቅ እንደሚያስፈልግም ተነግሯል።

ያነጋገርናቸው የውይይቱ ተሳታፊዎች ጥናቱ አበረታችና የኢትዮጵያን የአፈር መረጃ ቋት እንዲኖራት የሚያስችል መሆኑን ገልፀው በሀገሪቱ ዘላቂነት ያለው ምርታማነትን ለማምጣት ባለድርሻ አካላት በጋራ መስራት እንዳለባቸው ተናግረዋል