የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የ2011 በጀት አመት ማጠቃለያና የ2012 በጀት አመት መጀመሪያን በተመለከተ የከተሞች የማዘጋጃ ቤት አገልግሎት ግልፅ፤ቀልጣፈፋና ወጤታማ እንዲሁም ደረጃዉን የጠበቀ እንዲሆን እንዲሁም የዜጎችን ተጠቃሚነትና እርካታ ከፍ እንዲል ለማድረግ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ በመስራት ላይ እንደሚገኝ ገለፀ፡፡
በአዳማ ከተማ ከሶማሌ፤ከሃረሪና ቤኒሻንጉል ክልሎች እንዲሁም የድሬዳዋና አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደሮች የቢሮ ሃላፊዎና ባለድርሻ አካላት ዉይይት እያደረጉ ነዉ፡፡
በዉይይቱ ላይ ተገኝተዉ ንግግር ያደረጉት የኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ሚኒስትሯ ኢንጂነር አይሻ መኃመድ ለማዘጋጃ ቤቶች አገልግሎቶች አዳዲስ ደረጃዎችን በማዘጋጀትና በማፅደቅ በከተሞች እንዲተገበሩና የአገልግሎቶች አቅርቦትም እንዲሻሻል ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ነዉ ብለዋል፡፡
በማዘጋጃ ቤቶች የሚሰተዋለዉን የመልካም አስተዳደር ችግር ለመቅረፍና ለዜጎች ቀልጣፍ፤ ጊዜና ወጭ ቆጣቢ አገልግሎት በማቅረብ የዜጎችን እርካታ ከፍ ማድረግ በሚቻልበት ሁኔታነ ላይ ዉይይት እየተደረገ ነዉ፡፡
ጊዜና ጉልበት የሚያባክኑ አሰራሮችን ለማስቀረት የዜጎች ቻርተር ተዘጋጅቶ ተደራሽ እንዲሆንና ግልፅነትና ተጠያቀነት የሰፈነበት አሰራር እንዲኖር እየተሰራ መሆኑን አመልክተዋል፡፡
የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላንን በተከተለ አግባብ ብቻና የዜጎችን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ባማከለ መልኩ እንዲሆን ሰነድ አልባና ህገ ወጥ ይዞታዎችን ስርአት ለማስያዝ የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑም ተመልክቷል፡፡
በማዘጋጃ ቤቶች አገልግሎት አሰጣጥ ከሚታዩ ችግሮች መካከል የአመራር አካላት በህገ-ወጥ ተግባራት ላይ መሳተፍ ተጠቅሷል፡፡
ከተሞችን ከተቀመጠላቸዉ ደረጃ አኳያ ፅዱና ዉብ በማድረግ በኩል ብዙ ስራ ይቀራል ያሉት ሚኒስትሯ ነዋሪዎችን በማሳተፍና የጋራ ግንዛቤ በማስያዝ ዉጤታማ ተግባራትን ማከናወን እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡