11ኛዉ ሀገር አቀፍ የቡና ስንፖዚዬም በመደወላቡ ዩኒቨርሲቲ ተካሄደ

11ኛዉ ሀገር አቀፍ የቡና ስንፖዚዬም በመደወላቡ ዩኒቨርሲቲ ተካሄደ

በመዳወላቡ ዩኒቨርሲቲ የቡናን ምርትና ምርታማነትን በማሳደግና በዘርፉ የሚስተዋሉትን ተግዳሮቶች በመፍታት  ላይ ያተኮረ ሲምፖዚየም  ተካሄደ፡፡

ሲንፖዜዬሙ በመደወላቡ ዩኒቨርሲቲ፤ በኦሮሚያ ባህልና ቱሪዚም እና በአውሮፓ ህብረት የተዘጋጀ ሲሆን፤ የቡናን ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ፤ በአርሶ አደሩ ተጠቃሚነት ላይ ያተኮሩ ጥናታዊ ጽሁፎች ለዉይይት ቀርበዋል፡፡

በሲምፖዚየሙ በቀረቡት ጥናታዊ ጽሁፎች አገሪቷ ከቡና ምርት እምብዛም ተጠቃሚ አለመሆኗና በአገሪቷ የሚገኘውን የተፈጥሮ የቡና ምርት በማስተዋወቅ ረገድ የተሰሩት ስራዎች አናሳ መሆናቸው ተገልጿል።

በዘርፉ የሚታዩትን ተግዳሮቶች በማቃለልና የቡና እና ቱሪዝም በማስተሳሰር እምቅ የሆነውን የአገሪቷን የተፍጥሮ የቡና ሐብት በማስተዋወቅ ከዘርፉ የላቀ ተጠቃሚ ለመሆን የሚመለከታቸው አካላት በትኩረት መስራት ይኖርባቸዋል ተብሏል።

የኦሮሚያ ባህልና ቱሪዚም ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ አድማሱ ዋጋሪ እንደተናገሩት፤ አገሪቷ ከቡናው ዘርፍ የምታገኘውን ጥቅም ወደ ላቀ ደረጃ ለመሳደግ መንግስት በትኩረት ይሰራል ብለዋል።

የመደወላቡ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አቡበከር ከድር በበኩላቸው፤ ዩኒቨርሲቲው በቀጣይ ከሚመለከታቸዉ አካላትት ጋር በመሆን ቡና እና ቱሪዝምን በማስተሳሰር ሰፋፊ የምርምር ስራዎችን እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡

የባሌ ዞን የመንግስት ኮምንኬሽን ጉዳች ጸ/ቤት እንደዘገበው