በኢትዮጵያ እየተመናመነ ያለውን የደን ሽፋን ወደ ነበረበት ለመመለስ እና ረባዳ ቦታዎችን በደን ለመሸፍን የሚደረገው የክረምቱ መርሃ ግብር በርካታ መመስሪ ቤቶች ሰራተኞቻቸውን በማስተባበር ችግን እየተከሉ ይገኛሉ፡፡ የሰላም ሚኒስቴር ሰራተኞችም ሁለት ሺ ችግኞችን ተክለዋል፡፡
የሰላም ሚኒስትሯ ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል በዕለቱ እንደተናገሩት ለኢትዮጵያ ብሎም ለዓለም አሳሳቢ እየሆነ የመጣውን ከፍተኛ የካርበን ልቀት ለመቆጣጠር ችግኝ መትከል እና የተተከሉ ችግኞችን የመንከባከብ ሥራ መሰራት እንዳለበት ገልጸዋል፡፡
ወ/ሮ ሙፈሪያት እስከ ነሐሴ ድረስ የተለያዩ የሚኒስትር መስሪያ ቤቱ ተጠሪ ተቋማትን ጨምሮ 5 ሺ ችግኞችን ለመትከል ታስቦ እየተሰራ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
የሰላም ሚኒስቴር ሰራተኞች በበኩላቸው ችግኞችን በመትከል አየተስተዋለ ያለውን የአየር ንብረት ለውጥን መከላከል እንደሚያስፈልግ በመግለጽ በየጊዜው እየመጡም የተከሉትን ችግኞችን እንደሚንከባኩም ገልፀዋል፡፡