በእነ ብርጋዲየር ጀነራል ተፈራ ማሞ ጉዳይ መርማሪ ፖሊስ ያቀረበው የ14 ቀናት ጥያቄ ውድቅ ተደረገ

የባሕር ዳር ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት ፍርድ ቤቱ የእነ ብርጋዲየር ጀነራል ተፈራ ማሞን ጉዳይ ዛሬ ከሰዓት በኋላ ተመልክቷል፡፡

መርማሪ ፖሊስ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማሰባሰብ በሚል 14 ቀናት ጠይቆ የነበር ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ጥያቄውን ውድቅ አድርጎታል፡፡

ፍርድቤቱ በተጨማሪም እስከ ነሀሴ 13፣ 2011 ዓ.ም ድረስ የክስ መዝገባቸውን እንዲከፍትም ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ መስጠቱን አብመድ ዘግቧል ፡፡