በአዲስ አበባ የሞተር ብስክሌት ተሽከርካሪዎች ዳግም ወደ አገልግሎት ለማስገባት ምክክር ተካሄደ

በአዲስ አበባ ከተማ በከፊል የታገደውን የሞተር ብስክሌት ተሽከርካሪዎች አገልግሎት ዳግም ወደ ስራ እንዲገቡ የሚያሥችል ረቂቅ ላይ ውይይት ተካሂዷል።

ለውይይት የቀረበው ረቂቅ መመሪያ በአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የተዘጋጀ ነው፡፡

ረቂቁ ህግና ስርዓትን በማበጀትና ሞተረኞች በተሻለ ሁኔታ በማህበር እንዲደራጁ በማድረግ በከተማዋ የትራንስፖርት አገልግሎት ላይ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያስችል እንደሆነ ተብራርቷል፡፡

መመሪያው ሞተረኞች ከቦታ ቦታ በመንቀሳቀስ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሰጡ፣ ዕቃ ማመላለስን ጨምሮ ለግል ትራንስፖርት አገልግሎት መጠቀምን የሚፈቅድ ነው።

አገልግሎቱን ለመስጠት ከባለስልጣኑ ፈቃድ የሚወስዱት ሞተረኞችም በኮድ 3 የተመዘገቡት ብቻ ሲሆኑ በኦሮሚያና አማራ ክልል ሰሌዳ የሚጠቀሙ ሞተረኞች ግን በአዲስ አበባ አገልግሎት መስጠት አይችሉም ተብሏል።

መመሪያው የመከታተያና የመቆጣጠሪያ ስርዓት ቴክኖሎጂ /ጂ ፒ ኤስ/ በማስገጠም  አንድ ሞተረኛ አንድ አገልግሎት ብቻ እንዲሰጥ የሚፈቅድ መሆኑ ተገልጿል፡፡