የግብርና ሚኒስቴር ከቻይና አቻው 4 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ የግብርና መሳሪያዎች ተበረከቱለት

የቻይናው ግብርናና ገጠር ጉዳዮች ሚኒስቴር ከ4 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የግብርና መሳሪያዎችና ቁሳቁስ ለግብርና ሚኒስቴር አበርክቷል፡፡

ርክክቡ ሲካሄድ የቻይናው አምባሳደር ሚስተር ታን ጄይን እንዲሁም በኢትዮጵያ በኩል የግብርናው ሚኒስትር አቶ ዑመር ሁሴን ተገኝተዋል፡፡

ርክክብ ከተደረገባቸው መሳሪያዎች መካል ትራክተር፣ ዘር መዝሪያ ማሽን፣ የአፈር መከስከሻ ማሽን፣ የሩዝና ስንዴ መውቂያ ማሽን፣ የጥጥ ዘር መፈልፈያ፣ ጀነሬተሮች እና የቢሮ መገልገያ እቃዎች ይገኙባቸዋል፡፡

መሳሪያዎቹ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ለማስተዋወቅና ግብርናን ለማዘመን ከፍተኛ ሚና ያላቸው መሆኑ ተገልጿል፡፡

የቻይና መንግስት ለኢትዮጵያ ግብርና እድገት እያደረገ ላለው ድጋፍ የግብርናው ሚኒስትር አቶ ዑመር ሁሴን ከፍተኛ ምስጋና ማቅረባቸውን ከግብርና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡