የኦሮሚያ ክልል ም/ፕሬዝዳንትና የእንግሊዝ የዓለም አቀፍ ልማት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዩኒሌቨር ኩባንያን ጎበኙ

የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ የእንግሊዝ ዓለም አቀፍ ልማት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሎክ ሸርማ በኢስተርን እንደስትሪ ዞን የሚገኘውን የዩኒሌቨር ኩባንያን ጎብኝተዋል፡፡

አቶ ሽመልስ አብዲሳና የብሪታኒያ የዓለም አቀፍ የልማት ትብብር ሚኒስትር አሎክ ሻርማ በኢንዱስትሪ ዞኑ ባደረጉት ጉብኝትም የዩኒሊቨር ኩባንያ ስራዎችን ተዘዋውረው መመልከታቸውን የኦሮሚያ ክልል የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ አስታውቋል።

ዓለም አቀፍ ተቋም የሆነው ዩኒሊቨር ኩባንያ በዱከም በሚገኘው ኢስተርን ኢንደስትሪያል ዞን ውስጥ ለምግብነት እና ለመዋብያነት የሚያገለግሎ ምርቶችን እያመረተ ለገበያ በማቅረብ ላይ ይገኛል።

ኩባንያ ኢስተርን ኢንደስትሪያል ዞን ባለው ፋብሪካም ከዚህ ቀደም ክኖር የምግብ ማጣፈጫ፣ ላይፍ ቦይ የንፅህና መጠበቂያ ሳሙና እና ቫዝሊን ሎሽን እያመረተ ይገኛል። (ምንጭ:-የኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን ቢሮ0