በአማራ ክልል ከአምደወርቅ- ተኬዜ-እብናት የገጠር መንገድ ፕሮጀክት ተመረቀ

በአማራ ክልል የተገነባው አምደወርቅ-ተኬዜ-እብናት የገጠር መንገድ ፕሮጀክት በዛሬው ዕለት ተመርቆ ለትራፊክ ክፍት ሆነ፡፡

በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ተመስገን ጥሩነህን ጨምሮ፤ የተለያዩ የክልሉ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

የ124 ኪ.ሜ የሚሸፍነው መንገዱ በአካባቢው ያለውን የእንስሳትና የተለያዩ የግብርና ምርቶችን ወደ ገበያ ለማቅረብ የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡

በአካባው በኢኮኖሚ መነቃቃት ረገድ ጉልህ ሚና ከመጫወቱም ባሻገር የሁለቱን ዞኖች ህዝቦች ማህበራዊ ግንኙነት እንደሚያጠናክርም ተገልጿል፡፡