ሀገራዊ የሪፎርም ስራዎች በጠንካራ ማክሮ ኢኮኖሚ ሊደገፍ እንደሚገባ ተገለፀ

ሀገራዊ የሪፎርም ስራዎች ዘላቂና ጤናማ እንዲሆኑ በጠንካራ ማክሮ ኢኮኖሚ ሊደገፍ እንደሚገባ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ደመቀ መኮንን ገለፁ።

ሀገራዊ የሪፎርም ስራዎች ዘላቂና ጤናማ እንዲሆኑ በጠንካራ ማክሮ ኢኮኖሚ ሊደገፍ እንደሚገባ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ደመቀ መኮንን ገለፁ።

ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ የውይይት መድረክ መክፈቻ መርሃ ግብር ላይ የተገኙት አቶ ደመቀ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያውን ሁሉም ሊሳተፍበት እንደሚገባ ተናግረዋል።

ውይይቱ የሀገሪቱን ፈጣን እድገት ዘላቂ እንዲሆን ማስቻልና ለወጣቶች ሰፊ የስራ ዕድል ለመፍጠር ያለመ ነው።

የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራሙን ይዘት ለማበልፀግና አተገባበሩን ለማሳለጥ ሁሉም ገንቢ አስተዋጽኦ ማድረግ እንደሚገባቸው ነው አቶ ደመቀ የገለፁት።

በገንዘብ ሚኒስቴር በኩል የተዘጋጀው "ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻአያ" መድረክ ላይ የተለያዩ ምሁራን፣ የግል ዘርፍ ተዎካዮች፣ የተፎካካሪ ፓርቲ ተወካዮች እና የዘርፉ ተዋንያን ተካፍለዋል።

ምንጭ፦ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት