መንግስት የግብርና ዘርፉን በምርምር የበለጠ እንደሚደግፍ አስታወቀ

መንግስት የግብርና ስራዉን በምርምር ስራዎች የበለጠ እንደሚደግፍ የግብርና ሚንስቴር አስታወቀ፡፡

ባለፉት ዓመታት በኦሮሚያ፣ በአማራ፣ በትግራይና በደቡብ ክልሎች በክላስተር የግብርና ስራ ላይ ሲደረግ የነበረዉ ጥናት ይፋ ተደረገ፡፡

የግብርና ሚኒስትሩ አቶ ኡመር ሁሴን ለዋልታ እንደገለጹት፤ ምርምሩ ምን አይነት ማዳበሪያ ለምን አይነት ዘር፣ ምን አይነት መሬት ለምን አይነት ዘርና ከገበያ ጋር የተያያዙ ዝርዝር ሁኔታዎችን የለየ ነዉ ብለዋል፡፡ በክላስተር ግብርና እንደ ሀገር ባለዉ ስራ ላይ ያሉ ክፍተቶችን ማሳየት የቻለ ጥናት መሆኑንም ሚንስቴሩ አክለዉ ገልጸዋል፡፡

አቶ ኡመር እንዳሉት ከሆነ መንግስት የምርምር ስራን የግብርና ስራዉ አካል ካደረገ  የበለጠ ዉጤታማ መሆን ይቻላል ብለዋል፡፡

ከመንግስት ጋር ላለፉት 6 ዓመታት በጋራ ሲሰራ የቆየዉ “SYNERGOS” የኢትዮጵያ ዳይሬክተር አቶ አበራ ቶላ በበኩላቸዉ፤ ለጥናቱ ስራ ስኬት ከፌዴራል እስከ ክልል ድረስ የነበሩ ድጋፎች አስተዋጽኦ እንደነበራቸዉ ተናግረዋል፡፡

ለጥናቱ ዓላማ የሚዉል ቢል ኤንዲ ሚልንዳ ጌትስ ፋዉንዴሽን አንድ ሚልዮን ዶላር ድጋፍ አድርጓል፡፡