ኢትዮ-ቴለኮም የደንበኞቹን ፍላጎት የለማሻሻል የሚያስችል የሶስት ዓመት ስትራቴጅክ ዕቅድ ማዘጋጀቱን አስታወቀ

ኢትዮ-ቴለኮም የደንበኞቹን ፍላጎት የለማሻሻል የሚያስችል የሶስት ዓመት ስትራቴጅክ ዕቅድ ማዘጋጀቱን አስታውቋል፡፡

የስትራቴጅክ ዕቅዱ ኩባንያው ወደ ግል ይዞታ እንደሚዞር ታሳቢ ያደረገና ከሀምሌ 2011 ዓ.ም እስከ 2014 ዓ.ም ያለውን ጊዜ እንደሚሸፍን ተገልጿል፡፡

ኢትዮ-ቴሌኮም ለ125 አመታት በኢትዮጵያ አገልግሎት እየሰጠ የሚገኝ ሲሆን፣ የቴሌኮም ዘርፉን ለማሳደግና የደንበኞችን ፍላጎት ለማሻሻል የሚረዳ ስትራቴጅክ ዕቅድ ማዘጋጀቱንም ነው ያስታወቀው፡፡

የሶስት አመታት ስትራቴጅካዊ ዕቅዱ የፋይናንስ አቅሙን ማሳደግ፣ ምርጥ የደንበኞች ሁለንተናዊ ተሞክሮ መፍጠር፣ የአገልግሎትና ቴክኖሎጂ ልህቀት፣ የኦፕሬሽን ልህቀትና ተቋማዊ ገፅታ ማጠናከርን የትኩረት አቅጣጫ እንዳደረገ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራአስፈፃሚ ወይዘሪት ፍሬህይወት አያለው ገልጸዋል፡፡

ተቋሙ በ2012 በጀት ዓመት የአገልግሎት ጥራትን ለማሻሻል በአዲስ አበባና በክልሎች የ4G ኔትወርክ ግንባታ እንደሚያከናውንም ወይዘሪት ፍሬህይወት ተናግረዋል፡፡

በበጀት አመቱ የደንበኛ ብዛቱን በ16 በመቶ በመጨመር 50 ነጥብ 4 ሚሊየን ለማድረስ ማቀዱንም አስታውቀዋል፡፡

በተጨማሪም በተያዘው በጀት አመት ከ45 ነጥብ 4 ብሊየን የሚደርስ ገቢ ለመሰብሰብ ተቋሙ አቅዶ እየተንቀሳቀሰ ሲሆን፣ የህም የሀገሪቱ የማክሮ ኢኮኖሚና የዋጋ ግሽበት ታሳቢ ተደርጎ የታቀደ ነው ተብሏል፡፡