የደቡብ ክልል ምክር ቤት ዛሬ ማካሄድ በጀመረው 5ኛ ዙር 4ኛ አመት 9ኛ መደበኛ ጉባኤ የ2012 በጀት አመት 40 ቢሊዮን 56 ሚሊዮን 938 ሺህ ብር በጀት አጸደቀ፡፡
የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ሄለን ደበበ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር የምክር ቤቱ ጉባኤው ለመዘግየቱ ይቅርታ ጠይቀዋል።
በዋናነት በ3 አጀንዳዎች ላይ እየመከረ የሚገኘው ምክር ቤቱ የተለያዩ ሹመቶችንም ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡