የመስከረም ወር የነዳጅ ምርቶች መሸጫ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል

የመስከረም ወር የነዳጅ ምርቶች መሸጫ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል

የመስከረም ወር የነዳጅ ምርቶች መሸጫ ዋጋ ባለበት እንደሚቀጥል የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ በመስከረም ወር ከአውሮፕላን ነዳጅ ውጭ ሁሉም የነዳጅ ምርቶች ዋጋ ባለበት እንደሚቀጥልም አስታውቋል።

በዚህም የአውሮፕላን ነዳጅ በነሐሴ ወር ሲሸጥበት ከነበረው በሊትር 25 ብር ከ16 ሳንቲም በመስከረም ወር፥ 40 ሳንቲም በመጨመር በሊትር 25 ብር ከ56 ሳንቲም እንዲሸጥ ተወስኗል።

ሌሎች የነዳጅ ምርቶች መሸጫ ዋጋ ግን ባለበት እንደሚቀጥል ተገልጿል።