የዘንድሮው የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ በአራት የትምህርት አይነቶች ውጤት ብቻ ይወሰናል

የዘንድሮው የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ በአራት የትምህርት ዓይነቶች ውጤት ብቻ እንደሚወሰን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

እነዚህም የትምህርት ዓይነቶች እንግሊዝኛ፣ ሒሳብ፣ አፕቲቲዩድ እና ፊዚክስ በተፈጥሮ ሳይንስ እንዲሁም ጂኦግራፊን ጨምሮ በማህበራዊ ሳይንስ መሆናቸውን ነው የኢቢሲ ዘገባ ያመለከተው፡፡

ይህም የሆነው በሌሎቹ የትምህርት ዓይነቶች የውጤት ግሽበት በመታየቱ ነው ተብሏል።

በቀጣይ ደግሞ የመግቢያ መቁረጫ ነጥብ ይወሰናል ተብሏል።