ጠ/ሚ ዐብይ አህመድ ለጥቁር አንበሳ ሆስፒታል እድሳት ድጋፍ ላደረጉ ባለሃብቶች እውቅና ሰጡ

 

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በክረምት ለተደረገለት እድሳት የገንዘብ ድጋፍ ላደረጉ ባለሃብቶች እውቅና ሰጥተዋል።

ሌሎችም የነዚህን በጎ ፈቃደኞች አርአያነት በመከተል ህዝብን በነፃ የማገልገልና የመደገፍ ተግባርን ባህል እንዲያደርጉ ዶ/ር ዐቢይ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጴጥሮስ ሆስፒታል ያስገነባውን አዲስ ህንፃም በዛሬው እለት  መርቀዋል።

የጤና ሚኒስትሩ ዶክተር አሚር አማን እንዳሉትም በጥቁር አንበሳ የተደረገው በጎ ተግባር ለሌሎች ሆስፒታሎችም በጥሩ ተሞክሮነት የሚወሰድ ነው።

በቀጣይ ሌሎች ሆስፒታሎችም እድሳት እንዲደረግላቸው ሚኒስቴሩ ከባለ ሃብቱና ከማህበረሰቡ ጋር በትብብር እንደሚሰራ ማረጋገጣቸውን ኢዜአ ዘግቧል።