ም/ጠ/ሚ ደመቀ መኮንን የቀድሞ የኢትዮጵያ ባህር ሃይል ማህበር ተወካዮችን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ

የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የቀድሞ የኢትዮጵያ ባህር ሃይል ማህበር ተዎካዮችን በፅህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ።

የቀድሞ የኢትዮጵያ ባህር ሃይል ማህበር አባላት ካካበቱት ሙያ እና ልምድ አንፃር በቀጣይ በዘርፉ ሃገራዊ አቅም መሆን በሚችሉበት ጉዳዮች ዙሪያ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ ጋር ተወያይተዋል። መረጃው የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ነው፡፡