የባሕር ዳር – ዘማ ወንዝ – ፈለገ ብርሃን የአስፓልት ኮንክሪት መንገድ ተመረቀ

የባሕር ዳር – ዘማ ወንዝ – ፈለገ ብርሃን የአስፓልት ኮንክሪት መንገድ ተመረቀ።

የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ያስገነባው የባሕር ዳር- ዘማ ወንዝ- ፈለገ ብርሃን የአስፓልት ኮንክሪት መንገድ ዛሬ ተመርቋል፡፡

የባሕር ዳር- ዘማ ወንዝ- ፈለገ ብርሃን የአስፓልት ኮንክሪት መንገድ የጥራት ችግሮች እንዳሉበት የክልሉ የስራ ሃላፊዎች በቢቸና ከህዝብ ጋር ባደረጉት ውይይት ወቅት ተገልጿል።

የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን በነዋሪዎች የቀረበውን ቅሬታ ተቀብሎ መንገዱ ላይ ያሉ ጉድለቶችን እንደሚርም አስታውቋል፡፡

ዛሬ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት የሆነው መንገድ ከባሕር ዳር – አዲስ አበባ በደብረ ማርቆስ በኩል የሚደረገውን ጉዞ በ80 ኪሎ ሜትር የሚያሳጥር መሆኑ የተነገረ ሲሆን፤ መንገዱ በኢኮኖሚ እና በማኅበራዊ ትስስር ረገድ ከፍተኛ ፋይዳ እንደሚኖረው ታስቦ የተገነባና 175 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው መሆኑ ታውቋል፡፡ የአማራ መገናኛ ብዙሃን እንደዘገበው፤ አጠቃላይ የግንባታ ወጭውም 2 ቢሊዮን ብር ነው፡፡

በጎንጃ ሲሶ እነሴ ወረዳ የግንደ ወይን ከተማ ነዋሪው አቶ ጌትነት አየለ ‹‹የመንገዱ መጠናቀቅ የረዥም ጊዜ ጥያቄያችን ነበር፤ ወረዳው በስፋት የስንዴ እና የአትክልትና ፍራፍሬ አምራች በመሆኑ በሁልም አቅጣጫ ከገበያ ጋር እንዲተሳሰር ያደርገዋል›› ብለዋል።