ድርጅቱ 705 ሚሊዮን ቶን የእቃ ጭነት አገልግሎት ለመስጠት እየሰራ ነው

የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት በ2012 ዓ.ም 705 ሚሊዮን ቶን የእቃ ጭነት አገልግሎት ለመስጠት ማቀዱን የድርጀቱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሮባ መርገሳ በሰጡት መግለጫ አስታወቁ፡፡

ኢትዮጵያ አሁን ላይ 2 ነዳጅ ጫኝ እና 9 ሁለገብ አገልግሎት የሚሰጡ መርከቦች እንዳሏት የገለፁት ዋና ስራ አስፈፃሚዉ ፤ ባለፈዉ አመት የሀገሪቱን የወጪ ንግድ ተወዳዳሪነትን ለማረጋገጥ የተለያዩ ድጋፎችን ሲያደርግ መቆየቱንም ጠቅሰዋል፡፡

ድርጅቱ ባለፉት አመታት የገጠሙትን ዉስንነቶች ለመቅረፍም እንደሚሰራ ገልፆ ፤ ለመንግስት የልማት ድርጅቶች የዱቤ አገልግሎት ዉስጥ ሜቴክ 2 ቢሊየን ብር ውዝፍ እዳ እንዳለበትና በቀጣይ የሚመለስበት ወይም የሚሰረዝበት መንገድ ካለም የሚሰራ ይሆናል ብሏል፡፡

የአገልግሎት አሰጣጡን ለማሳደግ የአይ ሲ ቲ አጠቃቀምና የካይዘን ስራ አመራር ላይ በትኩረት  እንደሚሰራ ገልፆ፤  የቀጣይ ድርጅቱ ዋና ዋና እቅዶችንም አሳዉቋል፡፡

ቀደም ሲል የነበረዉ አሰራር አገልግሎት አሰጣጥ ላይ እንቅፋት ሆኖ የቆየዉን የባህር ወደብ አጠቃቀም አሰራርን ለማስተካልም ይሰራል ብለዋል ዋና ስራ አስፈፃሚዉ፡፡

የኢትዮጵያ ባሕር ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት በ2011 በጀት ዓመት የ1 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማግኘቱን አስታውቋል፡፡